Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ይህ​ንም ቃል በሰ​ማሁ ጊዜ ተቀ​ምጬ አለ​ቀ​ስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰ​ማ​ይም አም​ላክ ፊት እጾ​ምና እጸ​ልይ ነበር፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ይህን ነገር በሰማሁ ጊዜ አያሌ ቀናት ዐዘንሁ፤ ጾምሁ፤ በሰማይ አምላክም ፊት ጸለይሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እነዚህን ቃላት በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ። ለብዙ ቀኖች አዘንሁ፤ በሰማይ አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እኔም ይህን ሁሉ በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስኩ። ለብዙ ቀኖችም በጾምና በሐዘን ቈየሁ፤ ወደ እግዚአብሔርም እንዲህ ስል ጸለይኩ፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 1:4
22 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ስለ ሕፃኑ እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ለመነ፤ ዳዊ​ትም ጾመ፤ ገብ​ቶም በመ​ሬት ላይ ተኛ።


ልብ​ህን አላ​ደ​ነ​ደ​ን​ህ​ምና፥ እነ​ር​ሱም ለጥ​ፋ​ትና ለመ​ር​ገም እን​ዲ​ሆኑ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሰም​ተህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህን ቀድ​ደ​ሃ​ልና፥ በፊ​ቴም አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰሎ​ሞ​ንም ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መድ​ረክ ሠርቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ መካ​ከል ተክ​ሎት ነበር፤ በላ​ዩም ቆመ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ ፊት በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ር​ክኮ እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤


“የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ በይ​ሁ​ዳም ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ እን​ዳ​ስብ አደ​ረ​ገኝ፤


ዕዝ​ራም እያ​ለ​ቀ​ሰና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​ወ​ደቀ በጸ​ለ​የና በተ​ና​ዘዘ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ የወ​ን​ድና የሴት፥ የሕ​ፃ​ና​ትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰበ፤ ሕዝ​ቡም እጅግ አለ​ቀሱ።


ይህ​ንም ነገር በሰ​ማሁ ጊዜ ልብ​ሴ​ንና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዬን ቀደ​ድሁ፤ አዘ​ን​ሁም፤ የራ​ሴ​ንና የጢ​ሜ​ንም ጠጕር ነጨሁ፤ ደን​ግ​ጬም ተቀ​መ​ጥሁ።


በሠ​ር​ክም መሥ​ዋ​ዕት ጊዜ ልብ​ሴና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያዬ እንደ ተቀ​ደደ ሆኖ ከመ​ዋ​ረዴ ተነ​ሣሁ፤ በጕ​ል​በ​ቴም ተን​በ​ር​ክኬ ወደ አም​ላኬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጄን ዘረ​ጋሁ።


እኔም መልሼ፥ “የሰ​ማይ አም​ላክ ያከ​ና​ው​ን​ል​ናል፤ እኛም ንጹ​ሓን ባሪ​ያ​ዎቹ ተነ​ሥ​ተን እን​ሠ​ራ​ለን፤ እና​ንተ ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዕድል ፋን​ታና መብት፥ መታ​ሰ​ቢ​ያም የላ​ች​ሁም” አል​ኋ​ቸው።


ንጉ​ሡም፥ “ምን ትለ​ም​ነ​ኛ​ለህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አም​ላክ ጸለ​ይሁ።


ሰውስ በዘ​መኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እን​ዲሁ ያብ​ባል፤


አቤቱ፥ በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ የአ​ፌን ነገር ሁሉ ሰም​ተ​ኸ​ኛ​ልና፤ በመ​ላ​እ​ክት ፊት እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።


እር​ሱም፥ “እኔ ዕብ​ራዊ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ነኝ፤ ባሕ​ሩ​ንና የብ​ሱን የፈ​ጠ​ረ​ውን የሰ​ማ​ይን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ል​ካ​ለሁ” አላ​ቸው።


ከጉባኤው ርቀው የሚያዝኑትን፥ ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፣ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር።


ደስ ከሚ​ለው ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከሚ​ያ​ለ​ቅ​ሰው ጋርም አል​ቅሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos