“ከእኔ ጋር ና፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔርም እንደምቀና ታያለህ” አለው። ከእርሱም ጋር በሰረገላው አስቀመጠው።
ሮሜ 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ ምስክራቸው እኔ ነኝና፤ ነገር ግን ዐውቀው አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር ቀናተኞች እንደ ሆኑ ስለ እነርሱ መመስከር እችላለሁና፤ ቅናታቸው ግን ከዕውቀት የተነሣ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእግዚአብሔር ቅንዓት እንዳላቸው እመሰክርላቸዋለሁ ነገር ግን ቅንአታቸው በእውቀት ላይ የተመሠረተ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትክክለኛ ዕውቀት አለመሆኑ ነው እንጂ እነርሱ ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ ቅናት እንዳላቸው እኔ ራሴ እመሰክርላቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና። |
“ከእኔ ጋር ና፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔርም እንደምቀና ታያለህ” አለው። ከእርሱም ጋር በሰረገላው አስቀመጠው።
በዚያም ቀን እግዚአብሔር በፈጣኑ እባብ ደራጎን ላይ፥ በክፉውም እባብ ደራጎን ላይ ልዩ፥ ታላቅና ብርቱ ሰይፍን ያመጣል። በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድለዋል።
ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ደግሞም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።
እነርሱም ሰምተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉ፥ “ወንድማችን ሆይ፥ ከአይሁድ መካከል ያመኑት ስንት አእላፋት እንደ ሆኑ ታያለህን? ሁሉም ለኦሪት የሚቀኑ ናቸው።
እየጮሁም እንዲህ አሉ፥ “እናንተ የእስራኤል ወገኖች ሆይ፥ ርዱን፤ በየስፍራው ሕዝባችንን፥ ኦሪትንም፥ ይህንም ስፍራ የሚቃወም ትምህርት ለሰው ሁሉ የሚያስተምር እነሆ፥ ይህ ሰው ነው፤ አሁንም አረማውያንን ወደ መቅደስ አስገባ፤ ቤተ መቅደስንም አረከሰ።
ከጳውሎስም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “ይህ በሕይወት ሊኖር አይገባውምና እንዲህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው” እያሉ ጮሁ።
ጳውሎስም እንዲህ አላቸው፥ “እኔ አይሁዳዊ ሰው ነኝ፤ የቂልቅያ ክፍል በምትሆን በጠርሴስ ከተማ ተወለድሁ፤ በዚችም ከተማ ከገማልያል እግር ሥር ሆኜ አደግሁ፤ የአባቶችንም ሕግ ተማርሁ፤ እናንተ ሁላችሁ ዛሬ እንደምታደርጉትም ለእግዚአብሔር ቀናተኛ ነበርሁ።
የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያውቁአትምና በራሳቸውም ጽድቅ ጸንተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእግዚአብሔር ጽድቅ ግን መገዛት ተሳናቸው።
እግዚአብሔርን የሚመስለው የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው የዚህ ዓለም አምላክ ልባቸውን አሳውሮአልና።
በጨለማ ውስጥ “ብርሃን ይብራ” ያለ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የክብሩን ዕውቀት ብርሃን በልባችን አብርቶልናልና።
አሁንስ ደስ ማሰኘታችሁ ወዴት አለ? ቢቻላችሁስ ዐይናችሁንም እንኳ ቢሆን አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ፥ እኔ ምስክራችሁ ነኝ።