Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ገላትያ 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አሁ​ንስ ደስ ማሰ​ኘ​ታ​ችሁ ወዴት አለ? ቢቻ​ላ​ች​ሁስ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም እንኳ ቢሆን አው​ጥ​ታ​ችሁ ትሰ​ጡኝ እንደ ነበረ፥ እኔ ምስ​ክ​ራ​ችሁ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ለመሆኑ ያ ሁሉ ደስታችሁ የት ደረሰ? ቢቻላችሁ ዐይናችሁን ቢሆን እንኳ አውጥታችሁ የምትሰጡኝ እንደ ነበራችሁ እመሰክራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እንግዲህ መባረካችሁ የት አለ? ቢቻል ኖሮ ዐይኖቻችሁን እንኳ አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ እኔ እመሰክርላችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህ በፊት የነበራችሁ ደስታ ሁሉ የት ሄደ? ቢቻልስ ዐይኖቻችሁን እንኳ አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ እኔ ራሴ እመሰክርላችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እንግዲህ ደስ ማሰኘታችሁ ወዴት አለ? ቢቻልስ ዓይኖቻችሁን አውጥታችሁ በሰጣችሁኝ ብዬ እመሰክርላችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 4:15
17 Referencias Cruzadas  

በእ​ር​ሱም አማ​ካ​ኝ​ነት ወደ​ቆ​ም​ን​በት ወደ ጸጋው በእ​ም​ነት ተመ​ራን፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተስፋ እን​መ​ካ​ለን።


እጅግ እን​ደ​ሚ​ወ​ዳ​ች​ሁና ስለ እና​ንተ በሎ​ዶ​ቅ​ያና በኢ​ያራ ከተማ ስላ​ሉ​ትም እን​ደ​ሚ​ቈ​ረ​ቈር እኔ ምስ​ክሩ ነኝ።


እንዲሁም እያፈቀርናችሁ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማካፈል ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሳችንን ደግሞ እናካፍላችሁ ዘንድ በጎ ፈቃዳችን ነበረ፤ ለእኛ የተወደዳችሁ ሆናችሁ ነበርና።


ለሌላ ያይ​ደለ ለራሱ መመ​ኪያ እን​ዲ​ሆ​ነው ሁሉም ሥራ​ዉን ይመ​ር​ምር።


የመ​ን​ፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕ​ግ​ሥት፥ ምጽ​ዋት፥ ቸር​ነት፥ እም​ነት፥ ገር​ነት፥ ንጽ​ሕና ነው።


ልጆች፥ እንደ ገና የም​ጨ​ነ​ቅ​ላ​ችሁ ክር​ስ​ቶስ በል​ባ​ችሁ እስ​ኪ​ሣ​ል​ባ​ችሁ ድረስ ነው።


እኛ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነን የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ተስፋ እን​ድ​ና​ገኝ የአ​ብ​ር​ሃም በረ​ከት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ወደ አሕ​ዛብ ይመ​ለስ ዘንድ።


እነ​ርሱ ሲቻ​ላ​ቸው፥ ሳይ​ቻ​ላ​ቸ​ውም እን​ስጥ በማ​ለት ቈራ​ጦች ለመ​ሆ​ና​ቸው ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና።


የተ​ስፋ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይል በተ​ስፋ ያበ​ዛ​ችሁ ዘንድ በእ​ም​ነት ደስ​ታ​ንና ሰላ​ምን ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ቀኑ ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና፤ ነገር ግን ዐው​ቀው አይ​ደ​ለም።


በሥጋ ዘመ​ዶ​ችና ወን​ድ​ሞች ስለ​ሚ​ሆኑ እኔ ከክ​ር​ስ​ቶስ እለይ ዘንድ እጸ​ል​ያ​ለሁ።


በጭ​ን​ጫም ላይ የወ​ደ​ቀው ሰም​ተው ነገ​ሩን በደ​ስታ የሚ​ቀ​በ​ሉት ናቸው፤ ነገር ግን ለጊ​ዜው ያም​ናሉ እንጂ ሥር የላ​ቸ​ውም፤ መከ​ራም በአ​ገ​ኛ​ቸው ጊዜ ይክ​ዳሉ።


መከራ እቀ​በል በነ​በ​ረ​በት ጊዜ አል​ሰ​ለ​ቻ​ች​ሁ​ኝም፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ፥ እንደ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ተቀ​በ​ላ​ች​ሁኝ እንጂ በሰ​ው​ነቴ አል​ና​ቃ​ች​ሁ​ኝም።


እው​ነ​ቱን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ባላ​ጋራ ሆን​ኋ​ች​ሁን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios