ራእይ 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባሕርም ከሚኖሩ ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሲሶው ሞተ፤ የመርከቦችም ሲሶው ጠፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባሕሩም ውስጥ ከሚኖሩት ሕያዋን ፍጡራን አንድ ሦስተኛ ሞተ፤ የመርከቦችም አንድ ሦስተኛ ወደመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባሕርም ከሚኖሩ ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሲሶው ሞተ፤ የመርከቦችም ሲሶው ወደመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባሕር ውስጥ ከሚኖሩት ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሢሶው ሞተ፤ የመርከቦችም ሢሶ ወደመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባሕርም ከሚኖሩ ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሲሶው ሞተ የመርከቦችም ሲሶው ጠፋ። |
በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ገማ፤ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም፤ ደሙም በግብፅ ሀገር ሁሉ ሆነ።
ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት። የኬልቀዶን መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፤ ጠፍተዋልና፤ እንግዲህም ከኬጤዎን ሀገር አይመጡምና ማርከውም ይወስዱአቸዋልና።
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።
አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንም ሲሶው እንዳያበራ፥ እንዲሁም የሌሊት።
ፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።