ከከተማዪቱ በስተውጭ ያለውን የውኃውን ምንጭ ይደፍኑ ዘንድ ከአለቆቹና ከኀያላኑ ጋር ተማከረ፤ እነርሱም ምክሩን ወደዱ።
ራእይ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞችና በውሃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚነድድ ታላቅ ኮከብ በወንዞች አንድ ሦስተኛና በውሃ ምንጮች ላይ ከሰማይ ወደቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞችና በውሃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ የወደቀውም በወንዞች ሢሶና በውሃ ምንጮች ላይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦስተኛውም መልአክ ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፥ በወንዞችና በውኃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ። የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል። |
ከከተማዪቱ በስተውጭ ያለውን የውኃውን ምንጭ ይደፍኑ ዘንድ ከአለቆቹና ከኀያላኑ ጋር ተማከረ፤ እነርሱም ምክሩን ወደዱ።
“አንተ በንጋት የሚወጣ የአጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብም መልእክትን የላክህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ!
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።
በታላቅ ድምፅም “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውሃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት፤” አለ።
ፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።
ከይሁዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚያህሉ በኢጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሶምሶንን፥ “ገዢዎቻችን ፍልስጥኤማውያን እንደሆኑ አታውቅምን? ያደረግህብን ይህ ምንድን ነው?” አሉት። ሶምሶንም፥ “እንዳደረጉባችሁ እንዲሁ አደረግሁባቸው” አላቸው።