Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 9:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዐምስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይ ወደ ምድር የወደቀውንም ኮከብ አየሁ፤ ኮከቡም የጥልቁ ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁም ጉድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አምስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እነሆ፥ ከሰማይ ወደ ምድር የወደቀ አንድ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁ ጒድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አምስተኛውም መልአክ ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፥ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 9:1
20 Referencias Cruzadas  

ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞችና በውሃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ።


የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ፤ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።


“ወደ ጥል​ቁም ማን ይወ​ር​ዳል?” አት​በል፤ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነ​ሣው ክር​ስ​ቶስ ነው።


ሕያውም እኔ ነኝ፤ ሞቼም ነበርሁ፤ እነሆም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።


የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ።


ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፤ አሁንም የለም፤ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።


ወደ ጥል​ቁም ይገቡ ዘንድ እን​ዳ​ይ​ሰ​ድ​ዳ​ቸው ማለ​ዱት።


አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንም ሲሶው እንዳያበራ፥ እንዲሁም የሌሊት።


በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፤ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው።


ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ።


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሰይ​ጣ​ንን ከሰ​ማይ እንደ መብ​ረቅ ሲወ​ድቅ አየ​ሁት።


“አንተ በን​ጋት የሚ​ወጣ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ሆይ፥ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወደ​ቅህ! ወደ አሕ​ዛ​ብም መል​እ​ክ​ትን የላ​ክህ አንተ ሆይ፥ እን​ዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀ​ጠ​ቀ​ጥህ!


በለስም በብርቱ ነፋስ ተናውጣ ቃርያዋን ፍሬ እንደምትጥል የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ወደቁ፤


ምስክራቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል፤ ያሸንፋቸውማል፤ ይገድላቸውማል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios