ራእይ 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በኋላ አየሁ፤ እነሆ፤ በዙፋኑና በበጉ ፊት ማንም ሊቈጥራቸው የማይችል ከሕዝብ፣ ከነገድ፣ ከወገን፣ ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ነጭ ልብስ ለብሰው፣ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም ማንም ሊቆጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ሰዎች ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችን አየሁ፤ እነርሱ ከሕዝብና ከነገድ፥ ከወገንና ልዩ ልዩ ቋንቋ ከሚናገሩ ሁሉ የተውጣጡ ነበሩ፤ እነዚህ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤ |
መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ጌታ ሆይ! አንተ ኀይሌና ረዳቴ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ፤ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፥ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር ለምንም የማይረባቸውን ጣዖትን ሠርተዋል” ይላሉ።
ያንጊዜም ኢየሩሳሌምን የእግዚአብሔር ዙፋን ብለው ይጠሩአታል፤ አሕዛብም ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ወደ ኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉውን እልከኛ ልባቸውን ተከትለው አይሄዱም።
ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፤ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ።
የእስራኤልም ልጆች ቍጥር እንደማይሰፈርና እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፤ እንዲህም ይሆናል፤ “እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም” ተብሎ በተነገረበት በዚያ ስፍራ የሕያው አምላክ ልጆች ይባላሉ።
በመጀመሪያዋ ቀን የመልካም ዛፍ ፍሬ፥ የዘንባባውንም ቅርንጫፍ፥ የለመለመውንም ዛፍ ቅርንጫፍ፥ የወንዝም አኻያ ዛፍ ውሰዱ፤ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ፊት በየዓመቱ ሰባት ቀን ደስ ይበላችሁ።
በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፣ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።
በዚያን ጊዜም እጅግ ብዙ ሰዎች እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ ይላቸው ጀመረ፥ “አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፤ ይኸውም ግብዝነት ነው።
የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው “ሆሣዕና በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ፥ የእስራኤልም ንጉሥ ቡሩክ ነው” እያሉ ወጥተው ተቀበሉት።
ወንድሞቻችን፥ እና ዐዋቂዎች ነን እንዳትሉ ይህን ምሥጢር ልታውቁ እወዳለሁ፦ አሕዛብ ሁሉ እስኪገቡ ድረስ ከእስራኤል እኩሌቶችን የልብ ድንቍርና አግኝቶአቸዋልና።
ስለዚህም ደግሞ በብዛታቸው እንደ ሰማይ ኮከብ፥ እንደማይቈጠርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የነበሩት የሞተን ሰው እንኳ ከመሰለው ከአንዱ ተወለዱ።
እናንተ ግን፥ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደምትሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰማያት ወደ አለችው ኢየሩሳሌም፥ ደስ ብሎአቸው ወደሚኖሩ አእላፍ መላእክትም ደርሳችኋል።
ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።
በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።
አየሁም፤ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፤
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።