ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
መዝሙር 95:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር ለስሙ ክብርን አምጡ፤ መሥዋዕት ያዙ ወደ አደባባዮችም ግቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣ በመሪባም እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድረ በዳ፥ በመሪባና በማሳ እንዳደረጋችሁት፥ ልባችሁን አታጽኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያ በበረሓ ቦታ፥ በመሪባና በማሳ የቀድሞ አባቶቻችሁ እንዳደረጉት እልኸኞች አትሁኑ። |
ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፥ “እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን? ወይስ አይደለም?” ሲሉ እግዚአብሔርን ስለ ተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም “መንሱት” ደግሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እኒህ ሕዝብ እስከ መቼ ያስቈጡኛል? በፊታቸውስ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ እስከ መቼ አያምኑብኝም?
በግብፅ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ተአምራቴንና ክብሬን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈታተኑኝ፥ ቃሌንም ስላልሰሙ፥
“የሚያጕረመርሙብኝን እኒህን ክፉ ማኅበር እስከ መቼ እታገሣቸዋለሁ? ስለ እናንተ በእኔ ላይ የሚያጕረመርሙትን የእስራኤል ልጆች ማጕረምረምን ሰማሁ።
የእስራኤል ልጆች ተከራክረውበታልና ይህ ውኃ የክርክር ውኃ ተባለ። እርሱም ቅዱስ መሆኑ የተገለጠበት ይህ የክርክር ውኃ ነው።
በተሰበሰበውም ሕዝብ ፊት አንዳንዶች በእግዚአብሔር ትምህርት ላይ ክፉ እየተናገሩ ባላመኑ ጊዜ፥ ጳውሎስ ከእነርሱ ተለየ፤ ደቀ መዛሙርቱንም ይዞ ጢራኖስ በሚባል መምህር ቤት ሁልጊዜ ያስተምራቸው ነበር።
ነገር ግን ልቡናህን እንደ ማጽናትህ፥ ንስሓም እንደ አለመግባትህ መጠን የእግዚአብሔር እውነተና ፍርድ በሚገለጥበት ቀን መቅሠፍትን ለራስህ ታከማቻለህ።
ለሚናገረው እንቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነርሱ በደብረ ሲና የተገለጠላቸውን እንቢ ስለ አሉት ካልዳኑ፥ ከሰማይ ከመጣው ፊታችንን ብንመልስ እኛማ እንዴታ?
ዛሬ የሚባለው ቀን ሳለ ከእናንተ ማንም ቢሆን ወደ ኀጢአት በሚያደርስ ስሕተት እንዳይጸና ሁልጊዜ ሰውነታችሁን መርምሩ።
ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።
ግብጻውያንና ፈርዖንም ልባቸውን እንዳጸኑ ልባችሁን ለምን ታጸናላችሁ? በተዘባበቱባቸው ጊዜ ያወጡአቸው አይደሉምን? እነርሱም አልሄዱምን?