መዝሙር 90:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተኵላና በእባብ ላይ ትጫናለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ለአገልጋዮችህም ራራላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ለአገልጋዮችህ ራራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ቊጣህ እስከ መቼ ይቈያል? እባክህ ለአገልጋዮችህ ራራ! |
ግብፃውያንስ፦ ‘በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው’ ብለው ስለ ምን ይናገራሉ? ከመዓትህ ተመለስ፤ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ።
አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን አሳትኸን? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ፤
ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ ይቅር እላቸዋለሁ፥ ሁላቸውንም በርስታቸው፥ እያንዳንዳቸውንም በምድራቸው አኖራቸዋለሁ።
እኔም “አምልኮቴን ትተሃል አልሁ፤ ኤፍሬም ሆይ! እንዴት አደርግሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ እደግፍሃለሁ? እንዴትስ አደርግሃለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፤ ምሕረቴም ተገልጣለች።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፣ ቤቴ ይሠራባታል፣ በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ስለ አገልጋዮቹም ይራራል፤ በያሉበት መሳለቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥ ኀይላቸውም እንደ ደከመ፥ በጠላትም እጅ እንደ ወደቁ አይቶአልና።