መዝሙር 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው፥ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥ አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለተጨቈኑት መጠጊያ ነው፤ በመከራ ጊዜም መከላከያ አምባ ነው። |
እግዚአብሔርን የምትወድዱ፥ ክፋትን ጥሉ፤ እግዚአብሔር የጻድቃኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።
አምላካችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተቀደሰው ተራራ ይሰግዱለታል፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
ሰውም ቃሉን ይሰውራል፤ በውኃ እንደሚጠልቅም ይሰወራል፤ ክብሩም በደረቅ ምድር እንደሚፈስስ ውኃ በጽዮን ይገለጣል።
ብታምንበት ይቀድስሃል፤ እንደ ድንጋይ ዕንቅፋትም አያደናቅፍህም፤ እንደሚያድጥ ዓለትም አይሆንብህም፤ ሁለቱ የያዕቆብ ቤቶች ግን በኢየሩሳሌም በወጥመድና በአሽክላ ተይዘው ይኖራሉ።
“ነቢያትን የምትገድሊያቸው፥ ወደ አንቺ የተላኩትን ሐዋርያትንም የምትደበድቢያቸው ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፍዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ልሰበስባቸው ምን ያህል ወደድሁ? ነገር ግን እንቢ አላችሁ።
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።