ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በአሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።
መዝሙር 87:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የድኅነቴ አምላክ እግዚአብሔር፥ በቀንና በሌሊት በፊትህ ጮኽሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሠረቱን በተቀደሱ ተራሮች አቆመ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር። መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከተማውን በተቀደሰው ተራራ ላይ መሠረተ። |
ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በአሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።
እነሆ፥ የባሪያዎች ዐይኖች ወደ ጌቶቻቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁም ይቅር እስከሚለን ድረስ ዐይኖቻችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ ዋጋው ብዙ የሆነውን፥ የተመረጠውን፥ የከበረውንና መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም።
ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና፥ የሚቃጠለው መሥዋዕታቸውና ቍርባናቸውም በመሠዊያዬ ላይ የተመረጠ ይሆናል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፣ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፣ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።