መዝሙር 84:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ምሕረትህን አሳየን፥ አቤቱ፥ ማዳንህን ስጠን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኀይል ወደ ኀይል ይሸጋገራሉ፤ እያንዳንዱም በጽዮን ባለው አምላክ ፊት ይቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ ሲያልፉ የምንጭ ቦታ ያደርጉታል፥ የበልግም ዝናብ በረከትን ይሰጣልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጓዝ ላይ ሳሉ ብዙ ብርታትን ያገኛሉ፤ የአማልክትንም አምላክ በጽዮን ያዩታል። |
እነሆ፥ የባሪያዎች ዐይኖች ወደ ጌቶቻቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁም ይቅር እስከሚለን ድረስ ዐይኖቻችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
በጦራቸው ምድርን አልወረሱም፥ ክንዳቸውም አላዳናቸውም፤ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፤ ይቅር ብለሃቸዋልና።
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
ጽድቄን አመጣኋት፤ ከእኔ ዘንድ የምትገኝ መድኀኒትንም አላዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኀኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።
እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ይኖራል፤ እንደ ነፍስህም ፍላጎት ያጠግብሃል፤ አጥንትህንም ያለመልማል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።
በኤፍሬም ተራሮች ላይ የሚከራከሩ፦ ተነሡ፤ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጠሩባት ቀን ትመጣለችና።”
እነርሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያሉትን ስፍራዎች እባርካቸዋለሁ፤ ዝናቡንም በጊዜው አወርዳለሁ፤ የበረከትም ዝናብ ይሆናል።
በኢየሩሳሌም ላይ ከመጡት ከአሕዛብ ሁሉ የቀሩት ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ፥ የዳስ በዓልንም ያከብሩ ዘንድ በየዓመቱ ይወጣሉ።
በእግዚአብሔርም ሕግ እንደ ታዘዘ ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ስለ እርሱ መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡለት ዘንድ።
ከሄድሁና ቦታ ካዘጋጀሁላችሁም ዳግመኛ እመጣለሁ፤ እናንተም እኔ በአለሁበት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወስዳችኋለሁ።
በእኔ ያለውን፥ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍም ሁሉ ያስወግደዋል፤ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
የላከኝ የአብ ፈቃድም ይህ ነው፤ ከሰጠኝ ሁሉ አንድስ እንኳ ቢሆን እንዳይጠፋ ነው፤ ነገር ግን እኔ በኋለኛዪቱ ቀን አስነሣዋለሁ።
እኛስ ሁላችን ፊታችንን ገልጠን በመስተዋት እንደሚያይ የእግዚአብሔርን ክብር እናያለን፤ ከእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ተሰጠን መጠን የእርሱን አርአያ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንገባለን።
በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ይታይ፤
ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።