Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 14:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከሄ​ድ​ሁና ቦታ ካዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ች​ሁም ዳግ​መኛ እመ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተም እኔ በአ​ለ​ሁ​በት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋራ እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሄጄም ስፍራ ሳዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትኖሩ ዳግምኛ እመጣለሁ፤ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሄጄ ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ እኔ ባለሁበት እንድትኖሩ እንደገና መጥቼ እወስዳችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 14:3
20 Referencias Cruzadas  

እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ካለ ይከ​ተ​ለኝ፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ እኔ ባለ​ሁ​በት በዚያ ይኖ​ራ​ልና፤ እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ኝ​ንም አብ ያከ​ብ​ረ​ዋል።


እኔ እን​ደ​ም​ሄድ ወደ እና​ን​ተም እን​ደ​ም​መ​ለስ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን ሰም​ታ​ች​ኋል፤ ብት​ወ​ዱ​ኝስ ወደ አብ በመ​ሄዴ ደስ ባላ​ችሁ ነበር፤ እርሱ አብ ይበ​ል​ጠ​ኛ​ልና።


ወዴ​ትም እን​ደ​ም​ሄድ ራሳ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


አባት ሆይ፥ የሰ​ጠ​ኸኝ እነ​ዚህ እኔ ባለ​ሁ​በት አብ​ረ​ውኝ ይኖሩ ዘን​ድና የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ክብ​ሬን ያዩ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር ወድ​ደ​ኸ​ኛ​ልና።


እነ​ር​ሱም፥ “እና​ንተ የገ​ሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየ​አ​ያ​ችሁ ለምን ቆማ​ች​ኋል? ይህ ከእ​ና​ንተ ወደ ሰማይ ያረ​ገው ኢየ​ሱስ፥ ከእ​ና​ንተ ወደ ሰማይ ሲያ​ርግ እን​ዳ​ያ​ች​ሁት እን​ዲሁ ዳግ​መኛ ይመ​ጣል” አሏ​ቸው።


እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ከሆን ወራ​ሾቹ ነን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወራ​ሾች ከሆ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ወራ​ሾቹ ነን፤ በመ​ከራ ከመ​ሰ​ል​ነ​ውም በክ​ብር እን​መ​ስ​ለ​ዋ​ለን።


በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እኔስ ከዚህ ዓለም ልለይ፥ በከ​ክ​ር​ስ​ቶ​ስም ዘንድ ልኖር እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ለእኔ ይህ ይሻ​ለ​ኛል፤ ይበ​ል​ጥ​ብ​ኛ​ልም።


ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤


እን​ዲሁ ክር​ስ​ቶ​ስም የብ​ዙ​ዎ​ችን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ር​ጉት ያለ ኀጢ​አት ይገ​ለ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል።


እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos