መዝሙር 78:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማያውቁህም አሕዛብ ላይ ስምህንም በማትጠራ መንግሥት ላይ መዓትህን አፍስስ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሚቀጥለው ትውልድ እንዲያውቅ፣ እነርሱም በተራቸው ለልጆቻቸው፣ ገና ለሚወለዱትም እንዲነግሩ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚመጣ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተው ለልጆቻቸው እንዲናገሩ ነው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረገው ተከታዩ ትውልድ እንዲያውቀውና ለልጆቹም እንዲያስተምረው ነው። |
በግብፃውያንም ላይ የተዘባበትሁትን ሁሉ፥ ያደረግሁባቸውንም ተአምራቴን በልጆቻችሁና በልጅ ልጆቻችሁ ጆሮች ትነግሩ ዘንድ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስባቸው፤ እነርሱ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩና ለልጆቻቸውም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎኛልና በኮሬብ በተሰበሰባችሁ ጊዜ በፈጣሪያችሁ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ቆማችሁ ንገራቸው።