Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 78:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ይህም የሚቀጥለው ትውልድ እንዲያውቅ፣ እነርሱም በተራቸው ለልጆቻቸው፣ ገና ለሚወለዱትም እንዲነግሩ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሚመጣ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተው ለልጆቻቸው እንዲናገሩ ነው፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ይህንንም ያደረገው ተከታዩ ትውልድ እንዲያውቀውና ለልጆቹም እንዲያስተምረው ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በማ​ያ​ው​ቁ​ህም አሕ​ዛብ ላይ ስም​ህ​ንም በማ​ት​ጠራ መን​ግ​ሥት ላይ መዓ​ት​ህን አፍ​ስስ፤

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 78:6
11 Referencias Cruzadas  

ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤


ይህን ለልጆቻችሁ ተናገሩ፤ ልጆቻችሁ ለልጆቻቸው ይንገሩ፤ ልጆቻቸውም ለሚቀጥለው ትውልድ ይንገሩ።


ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤ ብርቱ ሥራህን ያውጃል።


ሥራህ ለአገልጋዮችህ፣ ክብርህም ለልጆቻቸው ይገለጥ።


ገና ላልተወለደ ሕዝብ፣ ጽድቁን ይነግራሉ፤ እርሱ ይህን አድርጓልና።


አምላክ ሆይ፤ ሳረጅና ስሸብትም አትተወኝ፤ ክንድህን ለመጪው ትውልድ፣ ኀይልህን ኋላ ለሚነሣ ሕዝብ ሁሉ፣ እስከምገልጽ ድረስ።


ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ፣ መከላከያ ዕርዶቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ መጠበቂያ ማማዎቿን እዩ።


እነዚህም ቀኖች በእያንዳንዱ ትውልድ፣ በእያንዳንዱ ቤተ ሰብ፣ በእያንዳንዱ አውራጃና በእያንዳንዱ ከተማ መታሰብና መከበር ይኖርባቸዋል፤ ይኸውም እነዚህ የፉሪም ቀኖች በአይሁድ ዘንድ ሳይከበሩ እንዳይቀሩ፤ መታሰቢያቸውም ከዘሮቻቸው መካከል እንዳይደመሰስ ነው።


“በምድሪቱ በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ እኔን ማክበር እንዲማሩ፣ ለልጆቻቸውም እንዲያስተምሩ ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ሕዝቡን በፊቴ ሰብስብ” ባለኝ ጊዜ፣ በኮሬብ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት የቆማችሁበትን ዕለት አስታውሱ።


ይኸውም ግብጻውያንን እንዴት አድርጌ እንደ ቀጣኋቸውና በመካከላቸውም ምልክቶቼን እንዴት እንዳደረግሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ እንድትነግሩና እኔ እግዚአብሔር መሆኔንም እንድታውቁ ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios