ረድኤቱንና ያሳያቸውን ተአምራቱን ረሱ፥
የእግዚአብሔርን ሥራ አስታውሳለሁ፤ የጥንት ታምራትህን በርግጥ አስታውሳለሁ፤
ይህ ድካሜ ነው አልሁ፥ የልዑል ቀኝ መለወጡ።
እግዚአብሔር ሆይ! ያከናወንካቸውን ታላላቅ ሥራዎች አስታውሳለሁ፤ ባለፉት ዘመናት ያደረግኻቸው ተአምራት ትዝ ይሉኛል።
ይስሐቅም በመሸ ጊዜ በልቡ እያሰላሰለ ወደ ሜዳ ወጥቶ ነበር፤ ዓይኖቹንም አቀና፤ እነሆም ግመሎች ሲመጡ አየ።
የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱንም፥ የአፉንም ፍርድ፤
የመረጥሃቸውን በጎነት እናይ ዘንድ፥ በሕዝብህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከርስትህም ጋር እንከብር ዘንድ።
ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፤ አምላካችንም ጻድቅ ነው።
አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው፥ ውረድም፤ ተራሮችን ዳስሳቸው፥ ይጢሱም።
የእግዚአብሔር ቃል ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁምና፥ በሕጉም ለመሄድ እንቢ አሉ፤
የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤ እንደ ክንድህም ታላቅነት የተገደሉትን ሰዎች ልጆች ጠብቃቸው።
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
በመሰንቆና በበገና፥ በከበሮና በእምቢልታም እየዘፈኑ የወይን ጠጅን ይጠጣሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፤ የእጁንም ሥራ አላስተዋሉም።