መዝሙር 75:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርድን ከሰማይ ታሰማለህ። ምድር ፈራች፥ ዝምም አለች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር እጅ ጽዋ አለ፤ በሚገባ የተቀመመና ዐረፋ የሚወጣው የወይን ጠጅ ሞልቶበታል፤ ይህን ከውስጡ ወደ ውጭ ገለበጠው፤ የምድር ዐመፀኞችም አተላውን ሳይቀር ይጨልጡታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህንን ያዋርዳል ያንንም ያከብራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤ በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤ እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል። |
የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የወይንን ፍለጋ ለሚከተሉስ አይደለምን? ግብዣ ከተደረገ ዘንድ በወይን አትስከሩ፥ ነገር ግን ከደጋግ ሰዎች ጋር በመደማመጥ ተነጋገሩ።
ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቁሚ፤ የሚያንገደግድሽን የቍጣውን ጽዋ ጠጥተሻልና፥ ጨልጠሽውማልና።
ለወገኑ የሚፈርድ አምላክሽ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ የሚያንገደግድሽን ጽዋ የቍጣዬንም ጽዋ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፥ “ያልተበረዘ የዚህን ቍጣ የወይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ አንተን የምሰድድባቸውን አሕዛብን ሁሉ አጠጣቸው።
ትጠጪዋለሽ፥ ትጨልጪውማለሽ፤ በዓላትሽንና መባቻዎችሽን እሽራለሁ፤ እኔ ተናግሬአለሁና ይላል እግዚአብሔር።
ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።