ከከተማዪቱም ወጥተው ገና ሳይርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ አለ፥ “ተነሥተህ ሰዎቹን ተከትለህ ያዛቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ በመልካሙ ፈንታ ስለምን ክፉን መለሳችሁ?
መዝሙር 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ ላደረጉብኝም ክፉን መልሼላቸው ብሆን፥ ጠላቶቼ ዕራቁቴን ይጣሉኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጎ ለዋለልኝ ክፉ መልሼ ብሆን፣ ጠላቴንም በከንቱ ዘርፌ ከሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህ አድርጌ ከሆነ፥ ዓመፃም በእጄ ቢኖር፥ |
ከከተማዪቱም ወጥተው ገና ሳይርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ አለ፥ “ተነሥተህ ሰዎቹን ተከትለህ ያዛቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ በመልካሙ ፈንታ ስለምን ክፉን መለሳችሁ?
በፋንታው ነግሠሃልና እግዚአብሔር የሳኦልን ቤት ደም ሁሉ መለሰብህ፤ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ለልጅህ ለአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ እነሆም፥ አንተ የደም ሰው ነህና በመከራ ተይዘሃል።”
ዳዊትም ከአውቴዘራማ ሸሸ፤ ወደ ዮናታንም መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “ምን አደረግሁ? ምንስ በደልሁ? ነፍሴንም ይሻት ዘንድ በአባትህ ፊት ጥፋቴና ኀጢአቴ ምንድን ነው?”
አቤሜሌክም መልሶ ንጉሡን፥ “ከባሪያዎቹ ሁሉ የታመነ፥ ለንጉሥም አማች የሆነ፥ የትእዛዝህ ሁሉ አለቃ፥ በቤትህም የከበረ እንደ ዳዊት ያለ ማን ነው?
ዳዊትም ሰዎቹን፥ “እግዚአብሔር የቀባው ነውና እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር አደርግ ዘንድ፥ እጄንም እጥልበት ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው” አላቸው።
ሳኦልም፥ “በድያለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዐይንህ ፊት ከብራለችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላደርግብህም፤ እነሆ፥ ስንፍና እንደ አደረግሁና፥ እጅግ ብዙም እንደ ሳትሁ ዐወቅሁ” አለ።
ነፍስህም ዛሬ በዐይኔ ፊት እንደ ከበረች እንዲሁ ነፍሴ በእግዚአብሔር ፊት ትክበር፤ ከመከራም ሁሉ ይሰውረኝ፤ ያድነኝም።”