ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን? መድኀኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤ ጸሎቴንም አድምጥ።
ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር።
አምላክ ሆይ! ጩኸቴን አድምጥ፤ ጸሎቴንም ስማ።
ራሴን አዋረድሁ እንጂ። ለነፍሴ ዋጋዋን ትሰጣት ዘንድ፤ የእናቱንም ጡት እንዳስጣሉት በቃሌ ጮኽሁ።
አቤቱ፥ በኀይሌ እወድድሃለሁ።
የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ጽድቄን ሰማኝ፥ ከጭንቀቴም አሰፋልኝ፤ ይቅር አለኝ፥ ጸሎቴንም ሰማኝ።
አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጠኝ፥ ልመናዬንም ቸል አትበለኝ።
አቤቱ፥ በቍጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመቅሠፍትህም አትገሥጸኝ።
አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም በኢየሩሳሌም ጸሎት ይቀርባል።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል።
በምንም አትጨነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማልዱም፤ እያመሰገናችሁም ልመናችሁን ለእግዚአብሔር ግለጡ።