ከጠላት ድምፅ፥ ከኀጢአተኛም ማሠቃየት የተነሣ፥ ዐመፃን በላዬ መልሰውብኛልና፥ ሊያጠፉኝም ተነሥተውብኛልና።
ባዕዳን ተነሥተውብኛልና፤ ግፈኞች ነፍሴን ሽተዋታል፤ እግዚአብሔርንም ከምንም አልቈጠሩም። ሴላ
አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥ በኃይልህም ፍረድልኝ።
ሞገደኞች አደጋ ሊጥሉብኝ ተነሡ፤ ጨካኞች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ፤ ስለ እግዚአብሔርም አያስቡም።
እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፤
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው፥ የከንፈሮቹንም ልመና አልከለከልኸውም።
በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዐመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፤
አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
እነሆ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ ጌታዬም ነፍሴን ያድናታል።
ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንም፥ እኔንም ስላላወቁ ነው።