ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።
በሀብታቸው የሚመኩትን፣ በብልጽግናቸውም የሚታመኑትን ለምን እፈራለሁ?
በደል ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?
እንዲሁም በሀብታቸው ብዛት የሚተማመኑና በብልጽግናቸው ብዛት የሚመኩ ክፉ ሰዎች ቢከቡኝስ ለምን እፈራለሁ?
ድሃውን ከምድር የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከመሬት ከፍ ከፍ የሚያደርግ፤
ከአለቆች ጋር ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያኖረው ዘንድ
እግዚአብሔር በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥ ክብሩም በምድር ሁሉ ላይ ነው።
ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አመሰግናለሁ፥ እዘምራለሁም።
በሰይፍ እጅ አልፈው ይሰጡ፥ የቀበሮዎችም ዕድል ፋንታ ይሁኑ።
የባለጠጋ ሀብት የጸናች ከተማ ናት፤ የዕውቀት ድህነት ግን የኀጢአተኞች ጥፋት ነው።
በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፤ ጻድቃንን የሚቀበል ግን ይለመልማል።
በእርሱ ላይ ዐይንህን ብታተኩር አታገኘውም፥ ለእርሱ የንስር ክንፍ ተዘጋጅቶለታልና። ወደሚቆምበትም ቤት ይመለሳልና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፤ ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ ባለጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤
በከነዓን እጅ የዐመፅ ሚዛን አለ፤ ቅሚያንም ይወድዳል።
ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ። ኢየሱስም ደግሞ መልሶ “ልጆች ሆይ! በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው።
ሰውነቴንም እንዲህ እላታለሁ፦ ሰውነቴ ሆይ፥ የሰበሰብሁልሽ ለብዙ ዓመታት የሚበቃሽ የደለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበልሽ።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።