እንዲህም አለ፥ “ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደ ምድር እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእግዚአብብሔር ስም የተባረከ ይሁን።”
መዝሙር 49:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተስ ተግሣጼን ጠላህ፥ ቃሌንም ወደ ኋላህ መለስኽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚሞትበትም ጊዜ ይዞት የሚሄደው አንዳች የለምና፤ ክብሩም ዐብሮት አይወርድም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ሀብት የቤቱም ክብር በበዛ ጊዜ አትፍራ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚሞትበት ጊዜ ምንም ነገር አይወስድም፤ ሀብቱም ከእርሱ ጋር ወደ መቃብር አይወርድም። |
እንዲህም አለ፥ “ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደ ምድር እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእግዚአብብሔር ስም የተባረከ ይሁን።”
ሲኦልም ሆድዋን አስፍታለች፤ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፤ የተከበሩና ታላላቅ ሰዎች ባለጠጎቻቸውና ድሆቻቸውም ወደ እርስዋ ይወርዳሉ።
እግዚአብሔርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከሥጋህ ለይተው ይወስዷታል፤ እንግዲህ ያጠራቀምኸው ለማን ይሆናል? አለው።
‘አባት አብርሃም ሆይ፥ እዘንልኝ፤ በዚች እሳት እጅግ ተሠቃይቻለሁና፥ ጣቱን ከውኃ ነክሮ ምላሴን ያቀዘቅዝልኝ ዘንድ አልዓዛርን ላከው’ ብሎ ተጣራ።