አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ ከወጡ ሕዝብም በቀሌን ተበቀል። ከዐመፀኛና ከሸንጋይ ሰው አድነኝ።
ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ፣ አምላክ ሆይ፤ ነፍሴም እንዲሁ አንተን ትናፍቃለች።
ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት።
አምላክ ሆይ! ዋላ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ።
የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፤
ልቤ መልካም ነገርን ተናገረ፥ እኔም ሥራዬን ለንጉሥ እናገራለሁ፤ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።
አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤ ባገኘን በታላቅ መከራም ጊዜ ረዳታችን ነው።
አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለአግዚአብሔር እልል በሉ።
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በመቅደሱ ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው።
አሕዛብ ሁላችሁ፥ ይህን ስሙ፤ በዓለም የምትኖሩም ሁላችሁ፥ አድምጡ፤
የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ምድርንም ጠራት፤ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ።
አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል ስማኝም፥ ድሃና ምስኪን ነኝና።
የድኅነቴ አምላክ እግዚአብሔር፥ በቀንና በሌሊት በፊትህ ጮኽሁ፤
አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘለዓለም እዘምራለሁ። ጽድቅህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ።
የቆሬ ልጆች አሴር፥ ሕልቃና፥ አብያሳፍ ናቸው፤ እነዚህ የቆሬ ልጆች ትውልድ ናቸው።
የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከኤልያብ ልጆች ከዳታንና ከአቤሮን፥ ከሮቤልም ልጅ ከፋሌት ልጅ ከአውናን ጋር ተናገረ።
ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ እነርሱን፥ ቤተ ሰቦቻቸውንም፥ ለቆሬም የነበሩትን ሰዎች ሁሉ፥ ከብቶቻቸውንም ሁሉ ዋጠቻቸው።
የቆሬ ልጆች ግን አልሞቱም።