Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 85:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል ስማ​ኝም፥ ድሃና ምስ​ኪን ነኝና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤ የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሆይ! ለምድርህ ምሕረትን አሳየህ፤ የያዕቆብን ዘር እንደገና አበለጸግህ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 85:1
13 Referencias Cruzadas  

የወ​ር​ቁና የብሩ ዕቃ​ዎች ሁሉ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሁሉ ሲሳ​ብ​ሳር ከባ​ቢ​ሎን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ከተ​መ​ለሱ ምር​ኮ​ኞች ጋር ወሰደ።


አቤቱ፥ ፍረ​ድ​ልኝ፥ ከጽ​ድቅ ከወጡ ሕዝ​ብም በቀ​ሌን ተበ​ቀል። ከዐ​መ​ፀ​ኛና ከሸ​ን​ጋይ ሰው አድ​ነኝ።


ተስ​ፋ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥራ እን​ዳ​ይ​ረሱ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም እን​ዲ​ፈ​ልጉ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የያ​ዕ​ቆ​ብን ድን​ኳን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለማ​ደ​ሪ​ያ​ውም እራ​ራ​ለሁ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በጕ​ብ​ታዋ ላይ ትሠ​ራ​ለች፤ አዳ​ራ​ሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖ​ሪያ ይሆ​ናል።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን በመ​ለ​ስሁ ጊዜ በይ​ሁዳ ሀገር በከ​ተ​ሞ​ችዋ፦ የጽ​ድቅ ማደ​ሪያ ሆይ! የቅ​ድ​ስና ተራራ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ የሚል ነገ​ርን እንደ ገና ይና​ገ​ራሉ።


“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሁን የያ​ዕ​ቆ​ብን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ እራ​ራ​ለሁ፤ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀ​ና​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ምድሩ ቀና፤ ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ለት።


“እነ​ሆም በዚያ ወራ​ትና በዚያ ዘመን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ።


ያን ጊዜ እኔ ከያ​ዕ​ቆብ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ደግ​ሞም ከይ​ስ​ሐቅ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን፥ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምም ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አስ​ባ​ለሁ።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፣ ቤቴ ይሠራባታል፣ በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos