ይኸውም እግዚአብሔር ስለ እኔ፦ ‘ልጆችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ፥ በፊቴም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በእውነት ቢሄዱ ከእስራኤል ዙፋን ሰው አይጠፋም’ ብሎ የተናገረውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።
መዝሙር 39:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን በትዕግሥት ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ተመልሶ ሰማኝ፥ የልመናዬንም ቃል ሰማኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ፣ “በአንደበቴ እንዳልበድል፣ መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ክፉዎችም በእኔ ዘንድ እስካሉ ድረስ፣ ልጓም በአፌ አስገባለሁ” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ ለኤዶታም፥ የዳዊት መዝሙር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ “ድርጊቴንና አንደበቴን ከኃጢአት እጠብቃለሁ፤ በአጠገቤ ክፉ ሰው በሚገኝበት ጊዜ ሁሉ አፌን እሸብባለሁ” ብዬ ቃል ገባሁ። |
ይኸውም እግዚአብሔር ስለ እኔ፦ ‘ልጆችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ፥ በፊቴም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በእውነት ቢሄዱ ከእስራኤል ዙፋን ሰው አይጠፋም’ ብሎ የተናገረውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።
ኢዩ ግን በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ይሄድ ዘንድ አልተጠነቀቀም፤ እስራኤልንም ካሳተው ከኢዮርብዓም ኀጢአት አልራቀም።
ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸው የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር አቆመ።
እርሱ ግን፦ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉውን ነገርስ አንታገሥምን?” በዚህ በደረሰበት ሁሉ ኢዮብ በእግዚአብሔር ፊት በከንፈሩ አልበደለም።
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ እንጨትና ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ ሥጋዬን ለአንተ እንዴት ልዘርጋልህ