Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 34:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔስ ባሠ​ቃ​ዩኝ ጊዜ ማቅ ለበ​ስሁ፥ ነፍ​ሴ​ንም በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፤ ጸሎ​ቴም ወደ ብብቴ ተመ​ለሰ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አንደበትህን ከክፉ ነገር ከልክል፤ ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሕይወትን የሚመኝ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እንግዲያውስ መጥፎ ነገር ከማውራትና ሐሰት ከመናገር ተቈጠቡ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 34:13
22 Referencias Cruzadas  

ሰው​ነቴ በላዬ ላይ ባለ​ቀች ጊዜ አቤቱ፥ መን​ገ​ዴን አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ በም​ሄ​ድ​ባት በዚ​ያች መን​ገድ ወጥ​መ​ድን ሰወ​ሩ​ብኝ።


አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።


“እርሱም ኀጢአት አላደረገም፤ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤”


አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።


አሮ​ጌ​ውን ሰው ከሥ​ራው ጋር ተዉት እንጂ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አቷሹ።


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል።


ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።


የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፥ የሚቸኩል ምስክር ግን ክፉ አንደበት አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በት​ዕ​ግ​ሥት ደጅ ጠና​ሁት፥ እር​ሱም ተመ​ልሶ ሰማኝ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ሰማኝ።


እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥


ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።


ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አይድንም፤ ክፋትን የሚያቀጣጥላትም ይጠፋባታል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ንሁ፥ አል​ፈ​ራም፥ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?


እር​ሱም፥ “ሕዝቤ ልጆች አይ​ደ​ሉ​ምን? ካል​ከ​ዱ​ኝስ ከመ​ከ​ራ​ቸው ሁሉ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ” አለ።


ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በቍጣ ትመ​ልስ ዘንድ፤ እን​ደ​ዚ​ህስ ያለ ነገር ከአ​ፍህ ታወጣ ዘንድ፤


በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ መል​ካ​ሙን ፈልጉ፤ ክፉ​ው​ንም አይ​ደ​ለም፤ እን​ዲሁ እና​ንተ እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios