የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።
ነፍሴም በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፤ በማዳኑም ሐሤት ታደርጋለች።
ነፍሴ ግን በጌታ ደስ ይላታል፥ በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።
ነፍሴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፤ በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።
ተናገረ፥ አንበጣም፥ ስፍር ቍጥር የሌለውም ኵብኵባ መጣ፥
ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መራራ ነው፥ መርገምንም ተሞልቶአል፤
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ተመልከተኝ፥ ለምን ተውኸኝ? የኀጢአቴ ቃል እኔን ከማዳን የራቀ ነው።
የኃጥእ ሞቱ ክፉ ነው ጽድቅንም የሚጠሉ ይጸጸታሉ።
መቃብራቸው ለዘለዓለም ቤታቸው ነው፥ ማደሪያቸውም ለልጅ ልጅ ነው፤ በየሀገራቸውም ስማቸው ይጠራል።
ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ፤ በጽዮን ልጅ በደጆችዋ፥ በማዳንህ ደስ ይለናል።
አሕዛብ በሠሩት በደላቸው ጠፉ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደ።
በእግዚአብሔርም እጅግ ደስ ይላቸዋል። ነፍሴም በእግዚአብሔር ሐሤት ታደርጋለች። ሽልማትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማቷም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የደስታንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና።
እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፣ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ምጽዋት፥ ቸርነት፥ እምነት፥ ገርነት፥ ንጽሕና ነው።
ሐናም ጸለየች፤ እንዲህም አለች፦ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በአምላኬ በመድኀኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህም ደስ ብሎኛል።