Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 35:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ነፍሴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፤ በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ነፍሴም በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፤ በማዳኑም ሐሤት ታደርጋለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነፍሴ ግን በጌታ ደስ ይላታል፥ በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የሕ​ይ​ወት ምንጭ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፤ በብ​ር​ሃ​ንህ ብር​ሃ​ንን እና​ያ​ለን።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 35:9
15 Referencias Cruzadas  

እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።


የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ደግነት፥ በጎነት፥ ታማኝነት፥


ይህም ሁሉ ቢሆን፥ እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በአምላኬ፥ በመድኃኒቴ ሐሤት አደርጋለሁ።


ፍርድህ ትክክለኛ ስለ ሆነ በጽዮን የሚኖሩ ሕዝቦች ደስ ይላቸዋል፤ በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ሐሴት ያደርጋሉ።


በቅዱስ ስሙም ስለምንታመን በእርሱ ደስ ይለናል።


አምላክ ሆይ! ኀይልን ስለ ሰጠኸው ንጉሥ ደስ ብሎታል፤ ድልን ስለ አቀዳጀኸውም ሐሴት ያደርጋል።


እኔ በማያቋርጥ ፍቅርህ እተማመናለሁ፤ በማዳንህ እደሰታለሁ።


ይህን ብታደርግልኝ፥ በጽዮን አደባባይ፥ ምስጋናህን ሁሉ ለሕዝብ እናገራለሁ፤ ስላዳንከኝም ደስታዬን እገልጣለሁ።


ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦ “ልቤ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤ ክብሬም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ ብሎአል፤ በማዳንህ ስለ ተደሰትኩ፤ በጠላቶቼ ላይ እሳለቃለሁ።


አሕዛብ በቈፈሩት ጒድጓድ ወደቁ፤ በደበቁት ወጥመድ ተያዙ።


ደስታዬ በእርሱ ስለ ሆነ እርሱም በማቀርብለት የተመስጦ ጸሎት ደስ ይበለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios