እኔስ ባሠቃዩኝ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥ ነፍሴንም በጾም አደከምኋት፤ ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ።
አንደበትህን ከክፉ ነገር ከልክል፤ ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ።
ሕይወትን የሚመኝ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?
እንግዲያውስ መጥፎ ነገር ከማውራትና ሐሰት ከመናገር ተቈጠቡ።
በእግዚአብሔር ፊት በቍጣ ትመልስ ዘንድ፤ እንደዚህስ ያለ ነገር ከአፍህ ታወጣ ዘንድ፤
ሰውነቴ በላዬ ላይ ባለቀች ጊዜ አቤቱ፥ መንገዴን አንተ ታውቃለህ፤ በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።
እግዚአብሔርን በትዕግሥት ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ተመልሶ ሰማኝ፥ የልመናዬንም ቃል ሰማኝ።
በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?
የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፥ የሚቸኩል ምስክር ግን ክፉ አንደበት አለው።
ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።
ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።
አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል።
ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።
ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አይድንም፤ ክፋትን የሚያቀጣጥላትም ይጠፋባታል።
አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።
እርሱም፥ “ሕዝቤ ልጆች አይደሉምን? ካልከዱኝስ ከመከራቸው ሁሉ አድናቸዋለሁ” አለ።
በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን ፈልጉ፤ ክፉውንም አይደለም፤ እንዲሁ እናንተ እንደ ተናገራችሁ ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።
አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ተዉት እንጂ፤ ወንድሞቻችሁን አቷሹ።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤
አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።
ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።
እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥
“እርሱም ኀጢአት አላደረገም፤ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤”