Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 12:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔር ሐሰተኛ ከንፈርን ይጸየፋል፤ በእውነተኞች ሰዎች ግን ደስ ይለዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ውሸተኛ ከንፈር በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር ሐሰተኛ አንደበትን ይጸየፋል፤ በእውነተኞች ሰዎች ግን ይደሰታል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 12:22
14 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም፥ “እኔ ደግሞ እን​ዳ​ንተ ነቢይ ነኝ፤ መል​አ​ክም፦ እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ወደ ቤትህ መል​ሰው ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ተና​ገ​ረኝ” አለው። ዋሽ​ቶም ተና​ገ​ረው።


ረድ​ኤቴ ሰማ​ይና ምድ​ርን ከፈ​ጠረ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።


ሐሰ​ትን የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሁሉ ትጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ደም አፍ​ሳ​ሹ​ንና ሸን​ጋ​ዩን ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​የ​ፋል።


አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤ እውነተኛ ሚዛን ግን በእርሱ ዘንድ የተመረጠ ነው።


ጠማማ መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን በፊቱ የተመረጡ ናቸው።


የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


የታመነች ከንፈር ለሰነፍ፥ የሐሰት ከንፈርም ለጻድቅ አትስማማውም።


ሽማ​ግ​ሌ​ውና ለፊት የሚ​ያ​ደ​ላው እርሱ ራስ ነው፤ ዐመ​ፅ​ንም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።


ነገር ግን የሚ​መ​ካው፦ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን፥ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ የማ​ደ​ርግ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሆ​ኔን በማ​ወ​ቁና በማ​ስ​ተ​ዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከንቱ ነገ​ርን ለሚ​ሰ​ሙት ሕዝቤ እየ​ዋ​ሻ​ችሁ ሞት የማ​ይ​ገ​ባ​ቸ​ውን ነፍ​ሳት ትገ​ድሉ ዘንድ፥ በሕ​ይ​ወ​ትም መኖር የማ​ይ​ገ​ባ​ቸ​ውን በሕ​ይ​ወት ታኖሩ ዘንድ ስለ ጭብጥ ገብ​ስና ስለ ቍራሽ እን​ጀራ ሕዝ​ቤን አር​ክ​ሳ​ች​ኋል።


እኔም ያል​መ​ለ​ስ​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን ልብ ወደ ዐመፃ መል​ሳ​ች​ኋ​ልና፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መን​ገድ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውን እጅ አበ​ር​ት​ታ​ች​ኋ​ልና፤


ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”


ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos