Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 34:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እንግዲያውስ መጥፎ ነገር ከማውራትና ሐሰት ከመናገር ተቈጠቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አንደበትህን ከክፉ ነገር ከልክል፤ ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሕይወትን የሚመኝ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔስ ባሠ​ቃ​ዩኝ ጊዜ ማቅ ለበ​ስሁ፥ ነፍ​ሴ​ንም በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፤ ጸሎ​ቴም ወደ ብብቴ ተመ​ለሰ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 34:13
22 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! ለአፌ ጠባቂ አኑር፤ በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።


ከመከራ ለማምለጥ የሚፈልግ፥ ክፉ ከመናገር ይቈጠባል።


እርሱ ምንም ኃጢአት አላደረገም፤ በአፉ ተንኰል አልተገኘበትም።


አንደበቱን ሳይቈጣጠር እግዚአብሔርን አመልካለሁ የሚል ሰው ራሱን ያታልላል፤ የእርሱም አምልኮ ከንቱ ነው።


አሮጌውን ባሕርይ ከነሥራው አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁት እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አትርሱ፤ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፥ ለመናገርና ለቊጣም የዘገየ ይሁን።


እኛ ሁላችን ብዙ ጊዜ እንሳሳታለን፤ በንግግሩ የማይሳሳት እርሱ ሰውነቱን መቈጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


ተጠንቅቆ የሚናገር ሕይወቱን ይጠብቃል። ግዴለሽ ተናጋሪ ግን ጥፋት ይደርስበታል።


እግዚአብሔር ሐሰተኛ አንደበትን ይጸየፋል፤ በእውነተኞች ሰዎች ግን ይደሰታል።


እውነት ግን ጸንታ ትኖራለች። ሐሰት ዘላቂነት የለውም፤


እኔ “ድርጊቴንና አንደበቴን ከኃጢአት እጠብቃለሁ፤ በአጠገቤ ክፉ ሰው በሚገኝበት ጊዜ ሁሉ አፌን እሸብባለሁ” ብዬ ቃል ገባሁ።


እንግዲህ ክፋትን ሁሉ፥ ማታለልን ሁሉ፥ ግብዝነትን፥ ቅናትን፥ ማንኛውንም ዐይነት ሐሜት አስወግዱ፤


አንደበትህ ሕይወትህን ሊያድን ወይም ሊያጠፋ ይችላል፤ ስለዚህ በአንደበትህ ወዳጆችን ብታፈራ ተደስተህ ትኖራለህ።


በሐሰት የሚመሰክር ሰው ሳይቀጣ አይቀርም፤ ሐሰትንም የሚናገር ጥፋት ያገኘዋል።


በከተማዋ ውስጥ ጥፋት አለ፤ አደባባዮችዋም በጭቈናና በአታላይነት የተሞሉ ናቸው።


እግዚአብሔር “በእርግጥ እነርሱ የእኔ ወገኖችና የማይዋሹ ልጆች ናቸው” አለ። ለእነርሱም አዳኛቸው ሆነ።


ዐመፀኞች ወድቀው ደብዛቸው ይጠፋል የደጋግ ሰዎች ትውልድ ግን ጸንቶ ይኖራል።


ይህንንም በማድረግህ በእግዚአብሔር ላይ መንፈስህን አነሣሥተሃል። እንዲህ ያለውን ሁሉ የወቀሳ ቃል እስከ መናገር ደርሰሃል።


በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉ ነገር አታድርጉ፤ ይህን ብታደርጉ ልክ እናንተ እንደምትሉት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios