አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።
እግዚአብሔር ከሰማይ ይመለከታል፤ የሰውንም ልጆች ሁሉ ያያል፤
ጌታ ከሰማይ ተመለከተ፥ የሰውንም ልጆች ሁሉ አየ።
እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ይመለከታል፤ የሰውንም ዘር ሁሉ ያያል፤
እግዚአብሔርም ምድርን እንደ ተበላሸች፥ ሥጋን የለበሱ ሁሉም በምድር ላይ መንገዳቸውን እንደ አበላሹ አየ።
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
እርሱ የኃጥኣን ሰዎች ሥራን ያውቃል፤ በደልንም ቢያይ ዝም ብሎ አይመለከትም፤ ይህንም አስተዋይ ሰው ያስተውላል።
እርሱም በሰማይ ያለውን ይመለከታል፥ በምድርም ያለውን ሁሉ ያውቃል።
እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥ በመንግሥቱም ሁሉን ይገዛል።
“ምላሳችንን እናበረታለን፤ ከንፈሮቻችን የእኛ ናቸው፥ ጌታችን ማን ነው?” የሚሉትን።
በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥ በልቡም እውነትን የሚናገር።
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ የአፌንም ቃል አድምጥ፤
እግዚአብሔር ይባርከናል፥ የምድርም ዳርቻዎች ሁሉ ይፈሩታል።
የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችንም ይመለከታሉ።
እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ እስኪመለከት ድረስ።
እኛን በሚቈጣጠር በእርሱ በዐይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።