Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 28:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እር​ሱም በሰ​ማይ ያለ​ውን ይመ​ለ​ከ​ታል፥ በም​ድ​ርም ያለ​ውን ሁሉ ያው​ቃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እርሱ የምድርን ዳርቻ ይመለከታልና፤ ከሰማይ በታች ያለውንም ሁሉ ያያል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እርሱም የምድርን ዳርቻ ሁሉ ይመለከታል፤ ከሰማይ በታች ያለውን ሁሉ ያያል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 28:24
15 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ በእ​ርሱ ዘንድ ፍጹም የሆ​ነ​ውን ያጸና ዘንድ ዐይ​ኖቹ በም​ድር ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታ​ሉና። አሁ​ንም ባለ​ማ​ወ​ቅህ በድ​ለ​ሃል፤ ስለ​ዚ​ህም ከዛሬ ጀምሮ ጦር​ነት ይሆ​ን​ብ​ሃል።”


በውኑ የሰው ዐይን አለ​ህን? ወይስ መዋቲ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ ታያ​ለ​ህን?


እርሱ የኃ​ጥ​ኣን ሰዎች ሥራን ያው​ቃል፤ በደ​ል​ንም ቢያይ ዝም ብሎ አይ​መ​ለ​ከ​ትም፤ ይህ​ንም አስ​ተ​ዋይ ሰው ያስ​ተ​ው​ላል።


እርሱ መን​ገ​ዴን የሚ​ያይ አይ​ደ​ለ​ምን? እር​ም​ጃ​ዬ​ንስ ሁሉ የሚ​ቈ​ጥር አይ​ደ​ለ​ምን?


እር​ሱን ወደ ሰማ​ያት ሁሉ ታች፥ ብር​ሃ​ኑ​ንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰ​ድ​ዳል።


የም​ድ​ርን ዳርቻ ይይዝ ዘንድ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ኃጥ​ኣ​ንን ያና​ውጥ ዘንድ።


ከሰ​ማይ በታች ያለ የም​ድ​ር​ንስ ስፋት አስ​ተ​ው​ለ​ሃ​ልን? መጠ​ኑም ምን ያህል እንደ ሆነ እስኪ ንገ​ረኝ!


የከ​ሰል እሳት እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠ​ል​በት ምድጃ ከአ​ፍ​ን​ጫው ጢስ ይወ​ጣል።


“ምላ​ሳ​ች​ንን እና​በ​ረ​ታ​ለን፤ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን የእኛ ናቸው፥ ጌታ​ችን ማን ነው?” የሚ​ሉ​ትን።


እና​ን​ተም ተራ​ሮች፥ እንደ ኮር​ማ​ዎች፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችስ፥ እንደ በጎች ጠቦ​ቶች ለምን ዘለ​ላ​ችሁ?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ከ​ናል፥ የም​ድ​ርም ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።


የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችንም ይመለከታሉ።


የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፣ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።


በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፤ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos