መዝሙር 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፥ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። |
በእውነት የተራሮች ኀይል፥ የኮረብቶችም ኀይል ሐሰት ነው፤ ነገር ግን የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ሰማይን ያጸናሁ፥ ምድርንም የፈጠርሁ፥ እጆችም የሰማይ ሠራዊትን ያቆሙ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እንዳትከተላቸውም እነርሱን አላሳየሁህም። ከግብፅ ምድርም ያወጣሁህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አትወቅ፤ ከእኔ በቀር የሚያድንህ የለምና።
እግዚአብሔርም አስቀድሞ ልጁን አስነሣላችሁ፤ ሁላችሁም ከክፋታችሁ እንድትመለሱ ይባርካችሁ ዘንድ ላከው።”
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።
ከዚህ በኋላ በሰማይ “ሃሌ ሉያ! በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችይቱን ታላቂቱን ጋለሞታ ስለ ፈረደባት፥ የባሪያዎቹንም ደም ከእጅዋ ስለ ተበቀለ፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኀይልም የአምላካችን ነው፤” ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ።