Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1-2 ከዚህ በኋላ በሰማይ “ሃሌ ሉያ! በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችይቱን ታላቂቱን ጋለሞታ ስለ ፈረደባት፥ የባሪያዎቹንም ደም ከእጅዋ ስለ ተበቀለ፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኀይልም የአምላካችን ነው፤” ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህ በኋላ የብዙ ሰዎችን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ማዳን፣ ክብርና ኀይል የአምላካችን ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከዚህ በኋላ በሰማይ የብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅን የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፦ “ሃሌ ሉያ! ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው፤”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ እንዲህ የሚል የብዙ ሰዎችን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ በሰማይ ሰማሁ “ሃሌ ሉያ! ማዳንና ክብር ኀይልም የአምላካችን ነው!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1-2 ከዚህ በኋላ በሰማይ፦ ሃሌ ሉያ፤ በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችይቱን ታላቂቱን ጋለሞታ ስለ ፈረደባት፥ የባሪያዎቹንም ደም ከእጅዋ ስለ ተበቀለ፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 19:1
23 Referencias Cruzadas  

ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”


አቤቱ፥ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያለው ሁሉ የአ​ንተ ነውና ታላ​ቅ​ነ​ትና ኀይል፥ ክብ​ርም፥ ድልና ጽንዕ የአ​ንተ ነው፤ ነገ​ሥ​ታ​ቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊ​ትህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’


እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።


ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳንና ኀይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸውየወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከሰ​ማ​ያት አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በአ​ር​ያም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤


ከን​ቱ​ነ​ት​ንና ሐሰ​ትን የሚ​ጠ​ብቁ፤ ይቅ​ር​ታ​ቸ​ውን ትተ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በተ​ቀ​ደሱ ቦታ​ዎች አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በኀ​ይሉ ጽናት አመ​ስ​ግ​ኑት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ መዝ​ሙር መል​ካም ነውና። ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ምስ​ጋና ማቅ​ረብ ያማረ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።


ማዳን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ በረ​ከ​ት​ህም በሕ​ዝ​ብህ ላይ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አዲስ ምስ​ጋ​ናን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ ምስ​ጋ​ና​ውም በጻ​ድ​ቃኑ ጉባኤ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም እጅግ የሚ​ወ​ድድ ሰው ብፁዕ ነው።


ንጉሥ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ምል ሁሉ ይከ​ብ​ራል፥ ዐመ​ፅን የሚ​ና​ገር አፍ ይዘ​ጋ​ልና።


የም​ድ​ራ​ቸ​ው​ንም ፍሬ ሁሉ በላ የተ​ግ​ባ​ራ​ቸ​ውን ሁሉ መጀ​መ​ሪያ በላ፥


አጥ​ፊ​ዎች ከሰ​ሜን ይመ​ጡ​ባ​ታ​ልና ሰማ​ይና ምድር፥ በእ​ነ​ር​ሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢ​ሎን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios