መዝሙር 28:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቃል ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር ሥራ ግድ ስለሌላቸው፣ ለእጆቹም ተግባራት ስፍራ ስላልሰጡ፣ እርሱ ያፈርሳቸዋል፤ መልሶም አይገነባቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጌታ ሥራ ወደ እጆቹም አደራረግ አላሰቡምና ያፈርሳቸዋል እንጂ አይሠራቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ለእግዚአብሔር አድራጎትና ለእጁ ሥራ ትኲረት ስለማይሰጡ እርሱ ይሰባብራቸዋል፤ እንደገናም አይገነባቸውም። |
አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ ሆይ፥ የባሪያህን ጆሮ ከፈትህ። አንተ፦ እኔ ቤት እሠራልሃለሁ አልህ፤ ስለዚህም ባሪያህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ በልቡ አሰበ።
ባሪያዬም ዳዊት እንዳደረገ፥ ያዘዝሁህን ሁሉ ብትሰማ፥ በመንገዴም ብትሄድ፥ በፊቴም የቀናውን ብታደርግ፥ ትእዛዜንና ሥርዐቴን ብትጠብቅ፥ ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤ ለዳዊትም እንደ ሠራሁለት የታመነ ቤትን እሠራልሃለሁ፤ እስራኤልንም ለአንተ እሰጥሃለሁ።
በአሮጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፤ ቀድሞ የሠራውንም አላያችሁም።
ዐይናችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ ይህን ሁሉ የፈጠረ ማን ነው? ከዋክብትንም በሙሉ የሚቈጥራቸው እርሱ ነው፤ በየጊዜያቸው ያመጣቸዋል፤ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በክብሩ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።
እኔ ምድርን ሠርቻለሁ፤ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማያትን አጽንቼአለሁ፤ ከዋክብቶቻቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።
ሰማይን የፈጠረ እግዚአብሔር፥ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፥ እንዲህ ይላል፥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።
“ሰማይ በላይ ደስ ይበለው፤ ደመናትም ጽድቅን ያዝንቡ፤ ምድርም መድኀኒትን ታብቅል፤ ጽድቅም በአንድነት ይብቀል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክ ፈጥሬሃለሁ።
በመሰንቆና በበገና፥ በከበሮና በእምቢልታም እየዘፈኑ የወይን ጠጅን ይጠጣሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፤ የእጁንም ሥራ አላስተዋሉም።
የእስራኤል ድንግል ሆይ እንደ ገና እሠራሻለሁ፤ አንቺም ትሠሪያለሽ፤ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ትወጫለሽ።
ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም ምንድን ነው? እኔ አደከምሁት፤ አጸናሁትም፤ እኔ እንደ ተወደደ አበባ አፈራዋለሁ፤ ፍሬህም በእኔ ዘንድ ይገኛል።
በያዕቆብ ላይ ጥንቆላ የለም፤ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በየጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል፦ እግዚአብሔር ምን አደረገ? ይባላል።
የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ እርሱም የዘለዓለም ኀይሉና ጌትነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ የፈጠረውን ፍጥረት በማሰብና በመመርመር ይታወቃል፤ መልስ የሚሰጡበትን ምክንያት እንዳያገኙ።
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው።