መዝሙር 25:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሕረትህ በዐይኔ ፊት ነው፥ በማዳንህም ደስ አለኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣ ከቶ አያፍሩም፤ ነገር ግን እንዲያው ያለ ምክንያት፣ ተንኰለኞች የሆኑ ያፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፥ በከንቱ የሚከዱ ያፍራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ የሚታመኑት ኀፍረት አይደርስባቸውም፤ ኀፍረት የሚደርስባቸው፥ በአንተ ላይ ለማመፅ የሚጣደፉት ናቸው። |
እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኀጢአት፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪን ጠየቀ።
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ እንጨትና ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ ሥጋዬን ለአንተ እንዴት ልዘርጋልህ
አቤቱ፥ የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ፥ ደስም ይበላቸው፤ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ፥ “ዘወትር እግዚአብሔር ታላቅ ነው” ይበሉ።
በዚያም ቀን፥ “እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፤ ያድናልም፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በመዳናችንም ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን” ይላሉ።
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”
እግዚአብሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆች ይሰናከላሉ፤ አያሸንፉም፤ ለዘለዓለምም የማይረሳ ጕስቍልናቸውን አላወቁምና ፈጽመው አፈሩ።