አቤቱ፥ ጽድቄን ስማኝ፥ ልመናዬንም አድምጠኝ፤ በተንኰለኛም ከንፈር ያልሆነውን ጸሎቴን አድምጠኝ፤
አምላክ ሆይ፤ መጠጊያዬ ነህና፣ በከለላህ ሰውረኝ።
የዳዊት ቅኔ። አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ።
አምላክ ሆይ! የምታመነው በአንተ ስለ ሆነ ጠብቀኝ፤
እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን።
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ ኀይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር የለውም።
የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ።
ከቍጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊቱም እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ በራ።
ይቅር በለኝ፥ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፤ ኀጢአት እስክታልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ።
አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬን ስማኝ፥ ጸሎቴንም አድምጠኝ።
አቤቱ፥ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ አትጣለኝም፤ ከሚከብቡኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥
ነፍሴን እንደ አንበሳ እንዳይነጥቋት፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር።
እግዚአብሔርም ምሕረቱን ይሰጣል፥ ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች።
ስምህን የሚወዱ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።
የጽድቅን ጎዳና ይጠብቃል፤ የሚፈሩትንም መንገድ ያጸናል።
ሙታንን በሚያስነሣቸው በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን በውስጣችን ለመሞት ቈርጠን ነበር።
ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፤ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።