በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤ አውታር በአለው መሣሪያና በእንዚራ አመስግኑት።
በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤ በባለአውታር መሣሪያና በእንቢልታ አመስግኑት።
በከበሮና በሽብሸባ አወድሱት፥ በባለ አውታር መሣሪያና በእምቢልታ አወድሱት።
በከበሮና በማሸብሸብ አመስግኑት፤ በክራርና በዋሽንት አመስግኑት።
በገናና መሰንቆ ይዘው ይዘምራሉ፤ በመዝሙራቸውም ደስ ይላቸዋል።
ስለዚህ ሕማሜ መሰንቆ፥ ልቅሶዬም በገና ሆነብኝ።
እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው። ይቅርታውም በሥራው ሁሉ ላይ ነው።
ስሙን በደስታ ያመሰግናሉ፥ በከበሮና በበገና ይዘምሩለታል።
ነፍሴም በእግዚአብሔር ትከብራለች፥ ገሮችም ይስሙ፥ ደስም ይበላቸው።
የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተአምራት እንድታዩ ኑ።
አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥ ወንዞች ቃሎቻቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ።
የአሮን እኅት ነቢይቱ ማርያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች፤ ሴቶችም ሁሉ በከበሮና በዝማሬ በኋላዋ ወጡ።
ጌታዬ ሆይ አንተ መድኀኒቴ ነህ፤ ስለዚህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አውታር ባለው ዕቃ አንተን ማመስገንን አላቋርጥም።”
ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፣ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፣ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።