መዝሙር 150:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ ወድሱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመለከት ድምፅ አወድሱት፥ በበገናና በመሰንቆ አወድሱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመለከት አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት። |
ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
ካህናቱም ሰበንያ፥ ኢዮሣፍጥ፥ ናትናኤል፥ ዓማሣይ፥ ዘካርያስ፥ በናያስ፥ አልዓዛርም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር። አብዲዶምና ኢያኤያም የእግዚአብሔር ታቦት በረኞች ነበሩ።
እንዲሁ እስራኤል ሁሉ በይባቤ፥ ቀንደ መለከትና እንቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም፥ በገናም እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።
ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ከፍ አድርገው ለማሰማት መለከትና ጸናጽል ለእግዚአብሔርም መዝሙራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤዶታም ልጆች ግን በረኞች ነበሩ።
ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶትምም ልጆች በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም የሚዘምሩ ሰዎችን ለማገልገል ለዩ፤ በየአገልግሎታቸውም ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑ በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ፥ “እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” እያሉ በአንድ ቃል ድምፃቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው በመለከትና በጸናጽል፥ በዜማም ዕቃ ሁሉ እግዚአብሔርን ባመሰገኑ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር የክብሩ ደመና የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው።
ደግሞ በደስታችሁ ቀን፥ በበዓላታችሁም ዘመን፥ በወርም መባቻ፥ በሚቃጠልም መሥዋዕታችሁና በደኅንነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶችን ንፉ፤ እነርሱም በአምላካችሁ ፊት ለመታሰቢያ ይሆኑላችኋል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።”