መዝሙር 149:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይለዋል፥ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያደርጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፥ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያድርጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝቦች በፈጣሪያችሁ ደስ ይበላቸው! የጽዮን ሕዝቦችም በንጉሣችሁ ሐሤት ያድርጉ! |
ሰላምን የሚያወራ፥ መልካም የምሥራችንም የሚናገር፥ መድኀኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፥ “አምላክሽ ነግሦአል” የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።
ፈጣሪሽ እግዚአብሔር ነው፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የእስራኤልም አምላክ ታዳጊሽ ነው፤ እርሱም በምድር ሁሉ እንደዚሁ ይጠራል።
እናንተ የጽዮን ልጆች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ ምግብን በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የበልጉንና የመከሩን ዝናብ ያዘንብላችኋልና።
አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፣ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል።
እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል፥ ጠላትሽንም ጥሎአል፣ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
እንዲህ እያሉ፥ “በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ የእስራኤል ንጉሥ ቡሩክ ነው፤ ሰላም በምድር፥ በአርያምም ክብር ይሁን።”
እነርሱ ግን፥ “አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮሁ። ጲላጦስም፥ “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አላቸው፤ ሊቃነ ካህናቱም፥ “ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ብለው መለሱ።
በዚያም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ብሉ፤ እጃችሁንም በምትዘረጉበት፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በባረካችሁ ነገር ሁሉ፥ እናንተና ቤተሰባችሁ ደስ ይበላችሁ።
ግዙራንስ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናገለግለውና የምናመልከው እኛ ነን፤ እኛም በኢየሱስ ክርስቶስ እንመካለን እንጂ በሥጋችን የምንመካ አይደለም።
እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።
እግዚአብሔር ለእርሱ ሕዝብ ያደርጋችሁ ዘንድ ተቀብሎአችኋልና፥ እግዚአብሔር ስለ ታላቅ ስሙ ሕዝቡን አይተውም።