Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 19:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ነገር ግን እነ​ዚ​ያን ልነ​ግ​ሥ​ባ​ቸው ያል​ወ​ደ​ዱ​ትን ጠላ​ቶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጡና በፊቴ ውጉ​አ​ቸው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ነገር ግን እኔ በላያቸው እንዳልነግሥ የፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡና በፊቴ ዕረዷቸው።’ ”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ነገር ግን እነዚያን በላያቸው እንድነግሥ ያልፈለጉትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው፤ በፊቴም እረዱአቸው።’”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በእነርሱ ላይ እንድነግሥ ያልፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ግን እዚህ አምጥታችሁ በፊቴ ግደሉአቸው!’ ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 19:27
23 Referencias Cruzadas  

የሀ​ገሩ ሰዎች ግን ይጠ​ሉት ነበ​ርና፥ ይህ በእኛ ላይ ሊነ​ግሥ አን​ሻም ብለው አከ​ታ​ት​ለው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ።


እን​ግ​ዲህ ጠላ​ቶቹ ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ወ​ድቁ ድረስ ይጠ​ብ​ቃል።


ንጉሡም ተቈጣ፤ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።


በእ​ር​ስዋ ላይ የተ​ጻ​ፈው ሁሉ ይፈ​ጸም ዘንድ እር​ስ​ዋን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜዋ ነውና።


ስፍራዋን ግን በሚያጥለቀልቅ ጎርፍ ፈጽሞ ያጠፋታል፥ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል።


በብ​ረት በትር ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”


የወ​ይኑ ባለ​ቤት በመጣ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ምን ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል? ይመ​ጣል፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ገባ​ሮች ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ወይ​ኑ​ንም ለሌ​ሎች ገባ​ሮች ይሰ​ጣል፤” ቃሉ​ንም ሰም​ተው፥ “አይ​ሆ​ንም፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግም” አሉ።


እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፣ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።


የጩ​ኸት ድምፅ ከከ​ተማ፥ ድም​ፅም ከመ​ቅ​ደስ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቹም ላይ ፍዳን የሚ​ያ​መጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድምፅ ተሰ​ም​ቶ​አል።


በሰ​ይፍ ስለት ይወ​ድ​ቃሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይማ​ረ​ካሉ፤ የአ​ሕ​ዛብ ጊዜ​ያ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ አሕ​ዛብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይረ​ግ​ጡ​አ​ታል።


ታያ​ላ​ችሁ፤ ልባ​ች​ሁም ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች፤ አጥ​ን​ታ​ች​ሁም እንደ ለም​ለም ሣር ትበ​ቅ​ላ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ለሚ​ፈ​ሩት ትታ​ወ​ቃ​ለች፤ ዐላ​ው​ያ​ን​ንም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።”


ሕዝ​ቡም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ሳኦል አይ​ን​ገ​ሥ​ብን ያሉ እነ​ማን ናቸው? እነ​ዚ​ያን ሰዎች አው​ጡ​አ​ቸ​ውና እን​ግ​ደ​ላ​ቸው” አሉት።


በእ​ሳት ከሚ​ቃ​ጠ​ሉና በው​ር​ደ​ታ​ቸው ከሚ​ነ​ድዱ በቀር በብ​ረት ብዛ​ትም ሆነ፥ በጦር ዘንግ ብዛት ሰው የሚ​ደ​ክ​ም​ባ​ቸው አይ​ደ​ሉም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios