ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፥ እጆቼ የሠርክ መሥዋዕትን አነሡ።
እነርሱ በልባቸው ክፉ ነገር ያውጠነጥናሉ፤ በየዕለቱም ጦርነት ይጭራሉ።
አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድነኝ፥ ከዓመፀኞች ሰዎች ጠብቀኝ
የእነርሱ ልብ ክፉ ዕቅዶችን ያቅዳል፤ ዘወትርም ጥልን ያነሣሣሉ።
እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅህ፥ እግዚአብሔር ነፍስህንም ይጠብቃት።
ልጨነቅ ቀርቤአለሁና፥ የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ።
በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ልመናዬንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም አድምጥ፥ ቸልም አትበለኝ፤ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶችም ሁሉ እንግዳ ነኝና።
ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ፥ ሰውነቴንም አጐበጡአት፤ ጕድጓድን በፊቴ ቈፈሩ፥ በውስጡም ወደቁ።
ለሕዝብህ ጭንቅን አሳየሃቸው፥ አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን።
ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና፥ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
ክፉን በሚያስብ ልብ ውስጥ ማታለል አለ፤ ሰላምን የሚወዱ ግን ደስ ይላቸዋል፥
እያደቡ ልባቸውን እንደ ምድጃ አዘጋጅተዋል፤ ጋጋሪያቸውም ሌሊቱን ሁሉ አንቀላፋ፤ በጠባም ጊዜ እንደ እሳት ነበልባል ይነድዳል።
በእግዚአብሔር ላይ በክፉ የሚያስብ፥ ክፋትን የሚመክር፥ ከአንተ ዘንድ ወጥቶአል።