ሥርዐትህን እጠብቅ ዘንድ የሚቀናስ ከሆነ መንገዴ ይቅና።
በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እግዚአብሔርም መለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ።
በተጨነቅሁ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፥ መለሰልኝ፥ አሰፋልኝም።
በተጨነቅሁ ጊዜ ጩኸቴን ወደ እግዚአብሔር አሰማሁ፤ እርሱም ሰማኝ፤ ነጻም አወጣኝ።
ያዕቆብም እጅግ ፈራ፤ የሚያደርገውንም አጣ። ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች ላሞችንም፥ ግመሎችንም፥ በጎችንም ሁለት ወገን አድርጎ ከፈላቸው፤
በእግዚአብሔር ኀይልን እናደርጋለን፤ እርሱም የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋል።
ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይምጣ?
አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥ መግቢያውም እስከ ዓለም ዳርቻ ነው፤ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።
አስተምርሃለሁ፥ በምትሄድባትም በዚች መንገድ አጸናሃለሁ። ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጸናለሁ።
አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ ያለውንም ምሳሌ እናገራለሁ።