መዝሙር 110:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፥ በፈቃዱም ሁሉ የተፈለገች ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰድዳል፤ “አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል፥ በጠላቶችህም መካከል ግዛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ኀያል ገዢነትህን ከጽዮን አንሥቶ ያሰፋዋል፤ እንዲህም ይልሃል፦ “በጠላቶችህ ላይ ንገሥ።” |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወንድምህ አሮንን፦ ‘በትርህን ውሰድ፤ በግብፅ ውኆች፥ በወንዞቻቸው፥ በመስኖዎቻቸውም፥ በኩሬዎቻቸውም፥ በውኃ ማከማቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ’ በለው፤ ደምም ይሆናል፤” በግብፅም ሀገር ሁሉ በዕንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ሆነ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወንድምህን አሮንን፦ ‘በትርህን ይዘህ በወንዞቹና በመስኖዎቹ፥ በውኃ ማከማቻዎቹም ላይ እጅህን ዘርጋ፤ ጓጕንቸሮችንም አውጣ’ ” በለው።
ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፥ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን” ይላሉ።
በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠንካራውም ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ! ብላችሁ አልቅሱለት።
ከተመረጡት ጫፎችዋም በትር እሳት ወጣች፤ ፍሬዋንም በላች፤ የነገሥታትም በትር ይሆን ዘንድ የበረታ በትር የለባትም።” ይህ ሙሾ ነው፤ ለልቅሶም ይሆናል።
ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ፤ እነሆም ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፤ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር።
ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።
በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
ወንጌልን ለማስተማር አላፍርምና፤ አስቀድሞ አይሁዳዊን፥ ደግሞም አረማዊን፥ የሚያምኑበትን ሁሉ የሚያድናቸው የእግዚአብሔር ኀይሉ ነውና።
ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።
ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።