ዘፀአት 8:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወንድምህን አሮንን፦ ‘በትርህን ይዘህ በወንዞቹና በመስኖዎቹ፥ በውኃ ማከማቻዎቹም ላይ እጅህን ዘርጋ፤ ጓጕንቸሮችንም አውጣ’ ” በለው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፣ “አሮንን፣ ‘በትርህን ይዘህ በምንጮች፣ በቦዮችና በኵሬዎች ላይ እጅህን ዘርጋ፤ ጓጕንቸሮችም በግብጽ ምድር ላይ እንዲወጡ አድርግ’ ” በለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ሙሴም ፈርዖንን፦ “እንቁራሪቶቹ ከአንተና ከቤቶችህ እንዲጠፋ፥ በዓባይ ወንዝም ብቻ እንዲቀሩ፥ ለአንተ፥ ለአገልጋዮችህና ለሕዝብህ መቼ እንድጸልይ ንገረኝ” አለው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እግዚአብሔርም ሙሴን “ጓጒንቸሮች ወጥተው መላውን የግብጽ ምድር ይሸፍኑ ዘንድ በወንዞች፥ በመስኖ ቦዮችና በኲሬዎች ሁሉ ላይ በትሩን እንዲዘረጋ ለአሮን ንገረው” አለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ “አሮንን፥ ‘በትርህን ይዘህ በወንዞቹና በመስኖቹ በውኃ ማከማቻዎቹም ላይ እጅህን ዘርጋ፤ በግብፅም አገር ላይ ጓጕንቸሮችን አውጣ፤ በለው።” Ver Capítulo |