መዝሙር 110 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 110 የዳዊት መዝሙር። 1 እግዚአብሔር ጌታዬን፣ “ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ፣ እስከማደርግልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ” አለው። 2 እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰድዳል፤ “አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ።” 3 ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ ከንጋት ማሕፀን፣ በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣ የጕልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ። 4 “እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዐት፤ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣ እግዚአብሔር ምሏል፤ እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም። 5 ጌታ በቀኝህ ነው፤ በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቅቃቸዋል። 6 በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ በየአገሩ ያሉትንም ራሶች ከስክሶ ሬሳ በሬሳ ያደርጋቸዋል። 7 መንገድ ዳር ካለች ፈሳሽ ውሃ ይጠጣል፤ ስለዚህ ራሱን ቀና ያደርጋል። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.