ሕይወትህን ከጥፋት የሚያድናት፥ በይቅርታውና በምሕረቱ የሚከልልህ፥
ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቋል፤ እህል መብላትም ዘንግቻለሁ።
ዘመኔ እንደ ጢስ አልቃለችና፥ አጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ተቃጥለዋልና።
እንደ ደረቀ ሣር ተሰባብሬ ደቀቅሁ፤ የምግብ ፍላጎቴም ጠፋ።
የቤቱም ሽማግሌዎች ተነሥተው ከምድር ያነሡት ዘንድ በአጠገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ከእነርሱም ጋር እንጀራ አልበላም።
ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤሊያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹም ኀጢአት ያለቅስ ነበርና ገብቶ እንጀራ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም።
“ነፍሴ ስለ ተጨነቀች ቃሌን በእንጕርጕሮ አሰማለሁ፤ ነፍሴም እየተጨነቀች በምሬት እናገራለሁ።
ቍርበቴ እጅግ ጠቈረ፥ አጥንቶቼም ከትኩሳት የተነሣ ተቃጠሉ።
ማንኛውንም መብል መቅመስ አይችልም። ሰውነቱ ግን መብልን ትበላ ዘንድ ትመኛለች።
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ፍላጻ በሥጋዬ ላይ ነው፤ መርዙም ደሜን ይመጥጣል። ለመናገር ስጀምርም ይወጋኛል።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጸና።
ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘለዓለምም አይቈጣም።
ፍላጾችህ ወግተውኛልና፥ እጅህንም በእኔ ላይ አክብደህብኛልና።
የሰማነውንና ያየነውን፥ አባቶቻችንም የነገሩንን፥ ለሚመጣ ትውልድ ከልጆቻቸው አልሰወሩም።
የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው።
ሄ። የሰገባውን ፍላጻዎች በኵላሊቴ ውስጥ ተከለ።
ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች።
በዚያም ሳያይ ሳይበላና ሳይጠጣ ሦስት ቀን ቈየ።