Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 10:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ዕዝ​ራም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ተነ​ሥቶ ወደ ኤሊ​ያ​ሴብ ልጅ ወደ ዮሐ​ናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምር​ኮ​ኞ​ቹም ኀጢ​አት ያለ​ቅስ ነበ​ርና ገብቶ እን​ጀራ አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከዚያም ዕዝራ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ክፍል ገባ፤ ምርኮኞቹ ታማኝነታቸውን ከማጕደላቸው የተነሣ ያለቅስ ነበር፤ በዚያም ምግብ አልቀመሰም፤ ውሃም አልጠጣም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሣ፥ ወደ ኤልያሺብ ልጅ ወደ ይሆሐናን ክፍል ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹ አለመታመን አዝኖ ነበርና በዚያ ገብቶ እንጀራ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ቀጥሎም ዕዝራ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ከነበረው ስፍራ በመነሣት የኤልያሺብ ልጅ ዮሐናን ወደሚኖርባቸው ክፍሎች ገባ፤ ምርኮኞቹ እምነት በማጓደል ስለ ፈጸሙትም በደል ሁሉ እያዘነ ሌሊቱን በዚያው አነጋ፤ እህልም ሆነ ውሃ አልቀመሰም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹም ኃጢአት ያለቅስ ነበርና ገብቶ እንጀራ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 10:6
16 Referencias Cruzadas  

ስለ ሠራ​ች​ሁት ኀጢ​አት ሁሉ፥ እር​ሱ​ንም ለማ​ስ​ቈ​ጣት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ የሆ​ነ​ውን ነገር ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ እንደ ፊተ​ኛው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ዳግ​መኛ ለመ​ንሁ፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፥ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም።


ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም በኤ​ል​ያ​ሴ​ብና በዮ​ሐዳ፥ በዮ​ሐ​ና​ንና በያ​ዱዕ ዘመን የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ተጻፉ፤ ካህ​ና​ቱም በፋ​ር​ሳ​ዊው በዳ​ር​ዮስ መን​ግ​ሥት ዘመን ተጻፉ።


ታላ​ቁም ካህን ኤል​ያ​ሴ​ብና ወን​ድ​ሞቹ ካህ​ናት ተነ​ሥ​ተው የበግ በር ሠሩ፤ ቀደ​ሱ​ትም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፤ እስከ መቶ ግን​ብና እስከ ሐና​ን​ኤል ግንብ ድረስ ቀደ​ሱት።


በዚ​ያም ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቅ​ሶ​ንና ዋይ​ታን፥ ራስን መን​ጨ​ት​ንና ማቅን መል​በ​ስን ጠራ።


ከት​እ​ዛ​ዙም አላ​ለ​ፍ​ሁም፤ ቃሉን በልቤ ሰው​ሬ​አ​ለሁ።


ከዋ​ነ​ኛ​ውም ካህን ከኤ​ል​ያ​ሴብ ልጅ ከዮ​ዳሔ ልጆች አንዱ ለሐ​ሮ​ና​ዊው ለሰ​ን​ባ​ላጥ አማች ነበረ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አባ​ረ​ር​ሁት።


ለሌ​ዋ​ው​ያን፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ንና ለበ​ረ​ኞቹ እንደ ሕጉ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና ዕጣ​ኑን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት፥ ለካ​ህ​ና​ቱም የሆ​ነ​ውን ቀዳ​ም​ያ​ቱን አስ​ቀ​ድሞ ያስ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ለት ነበር።


ኢያ​ሱም ዮአ​ቂ​ምን ወለደ፤ ዮአ​ቂ​ምም ኤሊ​ያ​ሴ​ብን ወለደ፤ ኤሊ​ያ​ሴ​ብም ዮሐ​ዳን ወለደ፤


ከእ​ር​ሱም በኋላ የዘ​ቡር ልጅ ባሮክ ከማ​ዕ​ዘኑ ጀምሮ እስከ ታላቁ ካህን እስከ ኤል​ያ​ሴብ ቤት መግ​ቢያ ድረስ ሌላ​ውን ክፍል ተግቶ ሠራ።


ዕዝ​ራም እያ​ለ​ቀ​ሰና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​ወ​ደቀ በጸ​ለ​የና በተ​ና​ዘዘ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ የወ​ን​ድና የሴት፥ የሕ​ፃ​ና​ትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰበ፤ ሕዝ​ቡም እጅግ አለ​ቀሱ።


ስለ ምር​ኮ​ኞ​ቹም መተ​ላ​ለፍ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ቃል የሚ​ፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥ​ዋ​ዕት ድረስ ዐዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ።


በዚ​ያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበረ፤ እን​ጀ​ራም አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም። በጽ​ላ​ቱም ዐሥ​ሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።


የም​ርኮ ልጆች ሁሉም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሰ​በ​ሰቡ ዘንድ ወደ ይሁ​ዳና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ዐዋጅ ነገረ


ሕይ​ወ​ት​ህን ከጥ​ፋት የሚ​ያ​ድ​ናት፥ በይ​ቅ​ር​ታ​ውና በም​ሕ​ረቱ የሚ​ከ​ል​ልህ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios