መዝሙር 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአተኞች እነሆ፥ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖቹን በስውር ይነድፉ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤ በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክፉዎች ትዕቢት ምስኪኖች ይሰደዳሉ፥ ባሰቡት ተንኰላቸው ተጠመዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ይታበያሉ፤ ድኾችንም ያሳድዳሉ፤ ለሌሎች በዘረጉት ወጥመድ ራሳቸው ይጠመዱ። |
በጽድቅ ገሥጸኝ፥ በምሕረትም ዝለፈኝ፥ የኀጢአተኛ ዘይትን ግን ራሴን አልቀባም፤ ዳግመኛም ጸሎቴ ይቅር እንዳትላቸው ነውና።
አንተም በልብህ፦ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፤ ዙፋኔንም ከሰማይ ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ በሰሜንም ዳርቻ በረዣዥም ተራሮች ላይ እቀመጣለሁ፤
የኢዮስያስ ልጅ ኣዛርያስ፥ የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፥ “ሐሰት ተናግረሃል፤ አምላካችን እግዚአብሔር፦ በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብፅ አትግቡ ብሎ አልላከህም፤